በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 136

ከይሖዋ የምናገኘው “ሙሉ ወሮታ”

ከይሖዋ የምናገኘው “ሙሉ ወሮታ”

(ሩት 2:12)

  1. 1. ይሖዋ ታማኝ የሆነ አምላክ ነው፤

    ከልብ ’ሚያመልኩትን ያውቃል።

    ታማኝነት ብዙ ነገር ሊያሳጣ

    እንደሚችልም ይረዳል።

    ቤተሰብን፣ ወዳጆችን ብታጣም፣

    አምላክ ይህን ሁሉ ያውቃል።

    አሁን ወንድሞችና እህቶችን፣

    ከዚያም ሕይወት ይሰጥሃል።

    (አዝማች)

    አምላካችን ልፋትህን አይቶ

    ወሮታውን ይክፈልህ አሟልቶ።

    በክንፎቹ ሥር ይከልልህ።

    ይሖዋ ታማኝ ነው፤ አይዋሽም ከቶ።

  2. 2. አንዳንዴ ሕይወት መራራ ይሆናል፤

    እንደ ሸክም ይጫነናል።

    የኑሮ ውጣ ውረድ ይከብደናል፤

    ኃይላችንም ይሟጠጣል።

    የመጽናናት አምላክ ይህን ይረዳል፤

    ጸሎታችንን ይሰማል።

    በቃሉ፣ በመንፈሱ ይረዳናል፤

    ታማኝ ወንድሞች ሰጥቶናል።

    (አዝማች)

    አምላካችን ልፋትህን አይቶ

    ወሮታውን ይክፈልህ አሟልቶ።

    በክንፎቹ ሥር ይከልልህ።

    ይሖዋ ታማኝ ነው፤ አይዋሽም ከቶ።

(በተጨማሪም መሳ. 11:38-40⁠ን እና ኢሳ. 41:10⁠ን ተመልከት።)