በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 12

ታላቁ አምላክ ይሖዋ

ታላቁ አምላክ ይሖዋ

(ዘፀአት 34:6, 7)

  1. 1. ይሖዋ አምላክ አንተ ታላቅ ነህ፤

    ውዳሴ ይገባሃል፤

    ትክክል ነው መንገድህ።

    አቻ የለውም ፍቅርህ፣ ጥበብህ፤

    የዘላለም አምላክ ነህ።

  2. 2. አየን ፍቅርህን፣ እንደምትወደን፤

    አፈር ብንሆንም ትቢያ

    በፊትህ ዋጋ ’ንዳለን።

    ’ሚያስፈልገንን ትሰጠናለህ፤

    ድንቅ ነው አመራርህ።

  3. 3. የ’ጅህ ሥራዎች፣ ፍጥረታት ሁሉ

    በመዝሙር ያወድሱህ፤

    ግርማህን ይናገሩ።

    ክብር ’ሚገባህ ታላቅ አምላክ ነህ።

    ከልብ እንዘምርልህ።

(በተጨማሪም ዘዳ. 32:4⁠ን፣ ምሳሌ 16:12⁠ን፣ ማቴ. 6:10⁠ን እና ራእይ 4:11⁠ን ተመልከት።)