በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 111

ለደስታችን ምክንያት የሆኑ ነገሮች

ለደስታችን ምክንያት የሆኑ ነገሮች

(ማቴዎስ 5:12)

  1. 1. ለደስታ አለን ብዙ ምክንያት፣

    ዋጋው እንደሚጨምር ሀብት።

    በብሔራት ውስጥ ያሉ ምርጦች፣

    ወደ’ኛ ጎርፈዋል ሕዝቦች።

    ደስታችን መሠረት ያለው ነው፤

    ከቃሉ የመነጨ ነው።

    ለዚህ ነው ሁሌም ’ምናነበው፤

    በሰማነው የምናምነው።

    ደስታችን ምንጊዜም አይጠፋም፤

    በልባችን እንዳለ ፍም።

    ብዙ ችግር ያጋጥመናል፤

    ይሖዋ ግን ያጸናናል።

    (አዝማች)

    አምላካችን ነው፣ ደስታችን፤

    ሥራዎቹም እርካታችን።

    ሐሳቦቹ ጥልቅ፣ ሥራዎቹም ድንቅ፣

    ነው ጥሩና ኃይሉ ታላቅ!

  2. 2. ድንቅ ነው ማየት ሥራዎቹን፣

    ሰማይ፣ ባሕርና ምድርን።

    ስናይ የፍጥረት ሥራዎቹን፣

    የ’ጁን ጥበብ ’ናደንቃለን።

    በደስታ እንመሠክራለን፤

    ያምላክ መንግሥት መቋቋሙን።

    የሚያመጣውንም በረከት፣

    ካጽናፍ አጽናፍ ’ናበስራለን።

    ጨለማው በብርሃን ይተካል፤

    የዘላለም ደስታ ቀርቧል።

    ሰላም ሲሰፍን በምድር ላይ

    የሰው ዘር ሐሴት ያደርጋል።

    (አዝማች)

    አምላካችን ነው፣ ደስታችን፤

    ሥራዎቹም እርካታችን።

    ሐሳቦቹ ጥልቅ፣ ሥራዎቹም ድንቅ፣

    ነው ጥሩና ኃይሉ ታላቅ!

(በተጨማሪም ዘዳ. 16:15⁠ን፣ ኢሳ. 12:6⁠ን እና ዮሐ. 15:11⁠ን ተመልከት።)