በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 101

በአንድነት አብሮ መሥራት

በአንድነት አብሮ መሥራት

(ኤፌሶን 4:3)

  1. 1. አምላክ ወደ ቤቱ ጠራን፤

    ከጨለማው ዓለም ወጣን።

    ሰላም አንድነት አገኘን፤

    በደስታም ተሞላን።

    አንድነታችንን

    እናደንቃለን።

    ያምላክ ሥራ በዝቶልናል።

    ልጁ ’ንዲመራን ተሹሟል።

    በታዛዥነት አንድ ሆነን፣

    ’ናገልግል ይሖዋን።

  2. 2. ስንጸልይ ላንድነታችን፣

    ስንጥር ደጎች ለመሆን፣

    ያድጋል፣ ይበዛል ፍቅራችን፤

    ደስታ፣ ሰላማችን።

    ሰላም ያስደስታል፤

    ልብ ያሳርፋል።

    ወንድሞችን ከወደድን፣

    እናገኛለን ሰላምን።

    ባምላክ እርዳታ ተባብረን

    ’ናገለግላለን።

(በተጨማሪም ሚክ. 2:12⁠ን፣ ሶፎ. 3:9⁠ን እና 1 ቆሮ. 1:10⁠ን ተመልከት።)