በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ንድፍ አውጪ አለው?

ጄሊፊሽ የሚወነጨፍበት መንገድ

ጄሊፊሽ የሚወነጨፍበት መንገድ

ጄሊፊሽ የሚባለው የዓሣ ዝርያ ከአጠቃላይ ክብደቱ 95 በመቶ የሚያህለው ውኃ ነው፤ ጄሊፊሾች የተለያየ መጠን ያላቸው ሲሆን አንዳንዶቹ ሰውነታቸው ከአንደኛው ጫፍ ወደ ሌላኛው ጫፍ ሲለካ ከ3 ሴንቲ ሜትር ያነሰ ርዝመት ሲኖረው ሌሎቹ ደግሞ ከ2 ሜትር የሚበልጥ ርዝመት ሊኖራቸው ይችላል። ብዙዎቹ የዚህ ዓሣ ዝርያዎች የሚጓዙት በጡንቻዎቻቸው አጋዥነት እየተወነጨፉ ነው፤ ይህንንም የሚያደርጉት የደወል ቅርጽ ያለውን አካላቸውን ልክ እንደ ጃንጥላ እጥፍ ዘርጋ በማድረግ ነው።

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ የፈሳሽንና የጋዝን እንቅስቃሴ የሚያጠኑ የሳይንስ ሊቃውንት፣ አንዳንድ ጄሊፊሾች ፈጣን ዋናተኞች ባይሆኑም አስደናቂ የሆነ የመወንጨፊያ መንገድ እንዳላቸው ተገንዝበዋል። እነዚህ የዓሣ ዝርያዎች ሰውነታቸው በተኮማተረ ቁጥር ቀለበት የመሰለ ቅርጽ ያለው የውኃ ሽክርክሪት በመፍጠር ውኃውን ወደታች ሲገፉት እነሱ ወደ ላይ ይወነጨፋሉ። ይህ ጄቶች ከሚወነጨፉበት መንገድ ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ልዩነቱ ጄቶችን የሚያስወነጭፈው ኃይል ወጥ መሆኑ ነው። ኒው ሳይንቲስት የተባለው መጽሔት ጄሊፊሾች ለመወንጨፍ ስለሚጠቀሙበት መንገድ ሲናገር እንዲህ ብሏል፦ “በጣም ቀላል ይመስላል። ያም ቢሆን የውኃ ሽክርክሪት የሚፈጠርበትን መንገድ በሒሳብ ስሌት ማስቀመጥ አስቸጋሪ ነው።”

ተመራማሪዎች ኃይል የሚቆጥቡ ባሕር ሰርጓጅ ተሽከርካሪዎችን ለመሥራት ሲሉ ጄሊፊሾች የሚወነጨፉበትን መንገድ በማጥናት ላይ ናቸው። አንድ ተመራማሪ ከጄሊፊሽ ጋር በሚመሳሰል መንገድ የሚወነጨፍ 1.2 ሜትር ርዝመት ያለው ባሕር ሰርጓጅ መርከብ ሠርቷል። ይህ ተሽከርካሪ የሚጠቀመው ኃይል በመደበኛው መቅዘፊያ የሚንቀሳቀሱ ባሕር ሰርጓጅ መርከቦች ከሚጠቀሙት ኃይል በ30 በመቶ ያንሳል። ከዚህም ሌላ ጄሊፊሾች የሚወነጨፉበትን መንገድ በማጥናት የሰው ልብ ስለሚመታበት መንገድ ተጨማሪ እውቀት ማግኘት ይቻላል። ደም በግራ በኩል ባለው የልብ ክፍል ውስጥ በሚዘዋወርበት ጊዜ ቀለበት መሰል ሽክርክሪት ይፈጥራል፤ ጤናማ ያልሆኑ ሽክርክሪቶች ከታዩ የልብ ሕመም መኖሩን አስቀድሞ ማወቅ ይቻላል።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? ጄሊፊሽ የሚወነጨፍበት መንገድ በዝግመተ ለውጥ የመጣ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[በገጽ 13 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

“ጄሊፊሾች” ቀለበት የመሰለ የውኃ ሽክርክሪት በመፍጠርና ውኃውን ወደታች በመግፋት ወደ ላይ ይወነጨፋሉ

[በገጽ 13 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

Photo: © JUNIORS BILDARCHIV/age fotostock; graphic: Courtesy of Sean Colin