በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ከዚህ ሥዕል ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?

ሁለተኛ ነገሥት 5:1, 9-16, 20-27⁠ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። በጥቅሱ ውስጥ ከተገለጹት መካከል የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሉ የተሟላ እንዲሆን ነጥቦቹን በመስመር ካገናኘህ በኋላ ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

3. ․․․․․

[ሰንጠረዥ]

(ጽሑፉን ተመልከት)

ለውይይት፦

ግያዝ ሁለት ጊዜ የዋሸው ምን ብሎ ነው?

ፍንጭ፦ 2 ነገሥት 5:22, 25⁠ን አንብብ።

ግያዝ እየዋሸ እንዳለ ማን ያውቅ ነበር?

ፍንጭ፦ 2 ነገሥት 5:25, 26⁠ን፤ 2 ዜና መዋዕል 16:9⁠ን እና ዕብራውያን 4:13⁠ን አንብብ።

መዋሸት የሌለብህ ለምንድን ነው?

ፍንጭ፦ ምሳሌ 12:22⁠ን እና ዮሐንስ 8:44⁠ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦

ሁለተኛ ነገሥት 5:1, 9-16, 20-27⁠ን በጋራ አንብቡ። የሚቻል ከሆነ አንደኛው ሰው ተራኪውን፣ ሁለተኛው ሰው ኤልሳዕን፣ ሦስተኛው ሰው ንዕማንን እና አገልጋዮቹን፣ አራተኛው ሰው ደግሞ ግያዝን ወክሎ እንዲያነብ አድርጉ።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 8 ሕዝቅያስ

ጥያቄ

ሀ. ሕዝቅያስ የይሁዳ ንጉሥ በሆነበት ወቅት ስንት ዓመቱ ነበር?

ለ. ይሖዋ በተአምራዊ መንገድ የሕዝቅያስን ዕድሜ በስንት ዓመት አራዝሞለታል?

ሐ. ይህን ዓረፍተ ነገር አሟላ። ሕዝቅያስ ታማኝ ስለነበረና ወደ ይሖዋ ስለ ጸለየ ይሖዋ አንድ መልአክ በመላክ ․․․․․ አሦራውያን ወታደሮችን እንዲገድል አድርጓል።

[ሠንጠረዥ]

4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ

ሕዝቅያስ የኖረበት ዘመን 700ዎቹ ዓ.ዓ. ገደማ

1 ዓ.ም.

98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ

[ካርታ]

በኢየሩሳሌም ኖሯል

አሦር

ኢየሩሳሌም

ሕዝቅያስ

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

የአምላክን ቤተ መቅደስ ያደሰና እንደገና የከፈተ፣ ለሐሰት አምልኮ የሚያገለግሉ ነገሮችን ያስወገደ እንዲሁም ሕዝቡ ፋሲካን እንዲያከብሩ ያበረታታ ታማኝ ንጉሥ። (2 ነገሥት 18:4፤ 2 ዜና መዋዕል 29:3፤ 30:1-6) አባቱ ንጉሥ አካዝ መጥፎ ሰው የነበረ ቢሆንም ሕዝቅያስ “ከእግዚአብሔር ጋር [ተጣብቋል]።”​—2 ነገሥት 18:6

መልስ

ሀ. 25 ዓመቱ።​—2 ነገሥት 18:1, 2

ለ. በ15 ዓመት።​—2 ነገሥት 20:1-6

ሐ. 185,000​—2 ነገሥት 19:15, 19, 35, 36

ሕዝቦችና አገሮች

4. ከርል እና ሺን እንባላለን፤ የ6 እና የ9 ዓመት ልጆች ስንሆን የምንኖረው በፊሊፒንስ ነው። በፊሊፒንስ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 62,000, 126,000 ወይስ 172,000?

5. የምንኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? በፊደሉ ላይ አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከፊሊፒንስ በጣም ይርቃል?

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

● “ቤተሰብ የሚወያይበት” መልሶች በገጽ 20 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ

1. የንዕማን ሠረገላ።

2. ብር የያዙ ከረጢቶች።

3. ልብሶች።

4. 172,000

5. መ።