በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

አካላዊ ጤንነት

አካላዊ ጤንነት

መጽሐፍ ቅዱስ የሕክምና መጽሐፍ አይደለም። ሆኖም ጤናማ ሕይወት እንድንመራ የሚረዱ ጠቃሚ ምክሮችን ይዟል። አካላዊ ጤንነትህን ለማሻሻል የሚረዱ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎችን እስቲ እንመልከት።

ሰውነትህን ተንከባከብ

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “የገዛ አካሉን የሚጠላ ማንም ሰው የለምና፤ ከዚህ ይልቅ ይመግበዋል እንዲሁም ይሳሳለታል።”—ኤፌሶን 5:29

ምን ማለት ነው? ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ አካላዊ ጤንነታችንን ለመንከባከብ የቻልነውን ሁሉ እንድናደርግ ያበረታታናል። አንድ ጥናት እንዳመለከተው አብዛኞቹ የጤና ችግሮች በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ከምናደርጋቸው ምርጫዎች ጋር የተያያዙ ናቸው። በመሆኑም ጥሩ ምርጫዎች በማድረግ ጤንነትህን ማሻሻል ትችላለህ።

ምን ማድረግ ትችላለህ?

  • አመጋገብ። ጤናማ ምግብ በመመገብና በቂ ውኃ በመጠጣት ከአመጋገብ ጋር በተያያዘ ጥሩ ምርጫ አድርግ።

  • አካላዊ እንቅስቃሴ። ወጣቶችም ሆኑ አረጋውያን እንዲሁም ከባድ ሕመምና የአካል ጉዳት ያለባቸው ሰዎች አካላዊ እንቅስቃሴ በማድረግ ጤንነታቸውን ማሻሻል ይችላሉ። ቤተሰቦችህና የጤና ባለሙያዎች እንቅስቃሴ እንድታደርግ ሊያበረታቱህ ቢችሉም እርምጃውን የምትወስደው ግን አንተ ራስህ ነህ።

  • በቂ እንቅልፍ ማግኘት። በቂ እንቅልፍ የመተኛት ልማድ ከሌለህ በከባድ በሽታዎች የመያዝ አጋጣሚህ ሰፊ ይሆናል። ብዙ ሰዎች በየዕለቱ በሚያደርጓቸው ምርጫዎች የተነሳ በቂ እንቅልፍ አያገኙም። ሆኖም በቂ እንቅልፍ ለማግኘት የሚያስችል ምርጫ ካደረግክ ጤንነትህን ማሻሻል ትችላለህ።

ጎጂ ልማዶችን አስወግድ

የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ፦ “ሥጋንና መንፈስን ከሚያረክስ ነገር ሁሉ ራሳችንን እናንጻ።”—2 ቆሮንቶስ 7:1

ምን ማለት ነው? እንደ ትንባሆ ያሉ ጎጂ ንጥረ ነገሮች የበሽታና የሞት ዋነኛ መንስኤ ናቸው፤ በመሆኑም እንዲህ ባሉ ነገሮች ሰውነታችንን አለመበከላችን ለጤንነታችን ይጠቅመናል።

ምን ማድረግ ትችላለህ? ማጨስ የምታቆምበትን ቀን ቁረጥ፤ ከዚያም በቀን መቁጠሪያህ ላይ ምልክት አድርግ። ያ ቀን ከመድረሱ በፊት ሲጋራዎችህን፣ መተርኮሻህን፣ መለኮሻህንና ከዚህ መጥፎ ልማድ ጋር የተያያዙ ሌሎች ዕቃዎችን በሙሉ አስወግድ። ሲጋራ ወደሚጨስበት አካባቢ አትሂድ፤ እንዲሁም ማጨስ ለማቆም እንደወሰንክ ለጓደኞችህ ንገራቸው።

ሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያዎች

በምትኖርበት አካባቢ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስ ሊሰጡህ ይችላሉ

ለደኅንነት ቅድሚያ ስጥ።

“አዲስ ቤት በምትሠራበት ጊዜ አንድ ሰው ከጣሪያህ ላይ ወድቆ በቤትህ ላይ የደም ዕዳ እንዳታመጣ በጣሪያህ ዙሪያ መከታ ሥራ።”​—ዘዳግም 22:8

ቁጣህን ተቆጣጠር።

“ቶሎ የማይቆጣ ሰው ትልቅ ማስተዋል አለው፤ ትዕግሥት የሌለው ሰው ግን ሞኝነቱን ይገልጣል።”​—ምሳሌ 14:29

ከልክ በላይ አትብላ።

“ያለልክ እንደሚሰለቅጡ ሰዎች አትሁን።”​—ምሳሌ 23:20