ለቆላስይስ ሰዎች የተጻፈ ደብዳቤ 3:1-25

  • አሮጌውና አዲሱ ስብዕና (1-17)

    • የአካል ክፍሎቻችሁን ግደሉ (5)

    • “ፍቅር ፍጹም የሆነ የአንድነት ማሰሪያ ነው” (14)

  • ለክርስቲያን ቤተሰቦች የተሰጠ ምክር (18-25)

3  ይሁን እንጂ ከክርስቶስ ጋር አብራችሁ ከተነሳችሁ+ ክርስቶስ በአምላክ ቀኝ+ በተቀመጠበት በላይ ያሉትን ነገሮች ፈልጉ።  አእምሯችሁ በምድር ባሉት ነገሮች ላይ ሳይሆን+ ምንጊዜም በላይ ባሉት ነገሮች ላይ እንዲያተኩር አድርጉ።+  እናንተ ሞታችኋልና፤ ሕይወታችሁም ከአምላክ ፈቃድ ጋር በሚስማማ ሁኔታ ከክርስቶስ ጋር ተሰውሯል።  ሕይወታችን የሆነው ክርስቶስ+ በሚገለጥበት ጊዜ እናንተም ከእሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።+  ስለዚህ በምድር ያሉትን የአካል ክፍሎቻችሁን ግደሉ፤+ እነሱም የፆታ ብልግና፣* ርኩሰት፣ ልቅ የሆነ የፍትወት ስሜት፣+ መጥፎ ፍላጎትና ጣዖት አምልኮ የሆነው ስግብግብነት ናቸው።  በእነዚህ ነገሮች ምክንያት የአምላክ ቁጣ ይመጣል።  እናንተም በቀድሞ ሕይወታችሁ በዚህ መንገድ ትኖሩ ነበር።+  አሁን ግን ቁጣን፣ ንዴትን፣ ክፋትንና+ ስድብን+ ሁሉ ከእናንተ አስወግዱ፤ ጸያፍ ንግግርም+ ከአፋችሁ አይውጣ።  አንዳችሁ ሌላውን አትዋሹ።+ አሮጌውን ስብዕና* ከነልማዶቹ ገፋችሁ ጣሉ፤+ 10  እንዲሁም ከፈጣሪው አምሳል ጋር በሚስማማ ሁኔታ+ በትክክለኛ እውቀት አማካኝነት እየታደሰ የሚሄደውን አዲሱን ስብዕና ልበሱ፤+ 11  በዚህ ሁኔታ ግሪካዊ ወይም አይሁዳዊ፣ የተገረዘ ወይም ያልተገረዘ፣ የባዕድ አገር ሰው፣ እስኩቴስ፣* ባሪያ ወይም ነፃ ሰው ብሎ ልዩነት የለም፤ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉም ነገር ነው፤ እንዲሁም በሁሉም ነው።+ 12  እንግዲህ የአምላክ ምርጦች፣+ ቅዱሳንና የተወደዳችሁ እንደመሆናችሁ መጠን ከአንጀት የመነጨ ርኅራኄን፣+ ደግነትን፣ ትሕትናን፣+ ገርነትንና+ ትዕግሥትን+ ልበሱ። 13  አንዱ በሌላው ላይ ቅር የተሰኘበት ነገር ቢኖረው+ እንኳ እርስ በርስ መቻቻላችሁንና በነፃ ይቅር መባባላችሁን ቀጥሉ።+ ይሖዋ* በነፃ ይቅር እንዳላችሁ ሁሉ እናንተም እንዲሁ አድርጉ።+ 14  ይሁንና በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ላይ ፍቅርን ልበሱ፤+ ፍቅር ፍጹም የሆነ የአንድነት ማሰሪያ ነውና።+ 15  በተጨማሪም አምላክ የጠራችሁ አንድ አካል እንድትሆኑና በሰላም እንድትኖሩ ስለሆነ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ።*+ እንዲሁም አመስጋኝ መሆናችሁን አሳዩ። 16  የክርስቶስ ቃል ከጥበብ ሁሉ ጋር በተትረፈረፈ ሁኔታ በውስጣችሁ ይኑር። በመዝሙራት፣ ለአምላክ በሚቀርብ ውዳሴና በአመስጋኝነት መንፈስ* በሚዘመሩ መንፈሳዊ ዝማሬዎች ትምህርትና ማበረታቻ* መስጠታችሁን ቀጥሉ፤+ በልባችሁም ለይሖዋ* ዘምሩ።+ 17  በቃልም ሆነ በተግባር የምታደርጉት ነገር ምንም ሆነ ምን አባት የሆነውን አምላክ በኢየሱስ በኩል እያመሰገናችሁ ሁሉንም ነገር በጌታ ኢየሱስ ስም አድርጉት።+ 18  ሚስቶች ሆይ፣ የክርስቶስ ተከታዮች ሊያደርጉት የሚገባ ስለሆነ ለባሎቻችሁ ተገዙ።+ 19  ባሎች ሆይ፣ ሚስቶቻችሁን መውደዳችሁን ቀጥሉ፤+ መራራ ቁጣም አትቆጧቸው።*+ 20  ልጆች ሆይ፣ በሁሉም ነገር ለወላጆቻችሁ ታዘዙ፤+ እንዲህ ማድረጋችሁ ጌታን ያስደስተዋልና። 21  አባቶች ሆይ፣ ቅስማቸው እንዳይሰበር* ልጆቻችሁን አታበሳጯቸው።+ 22  ባሪያዎች ሆይ፣ ሰውን ለማስደሰት ብላችሁ ሰብዓዊ ጌቶቻችሁ በሚያዩአችሁ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በቅን ልብ ተነሳስታችሁ ይሖዋን* በመፍራት ጌቶቻችሁ ለሆኑት በሁሉም ነገር ታዛዥ ሁኑ።+ 23  የምታደርጉትን ሁሉ ለሰው ሳይሆን ለይሖዋ* እንደምታደርጉት በማሰብ በሙሉ ነፍሳችሁ* አድርጉት፤+ 24  ከይሖዋ* ዘንድ እንደ ሽልማት የምትቀበሉት ውርሻ እንዳለ ታውቃላችሁና።+ ጌታችንን ክርስቶስን እንደ ባሪያ አገልግሉ። 25  መጥፎ ነገር የሚሠራ የእጁን እንደሚያገኝ የተረጋገጠ ነው፤+ ደግሞም አድልዎ የለም።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ግሪክኛ፣ ፖርኒያ። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ቃል በቃል “ሰው።”
“እስኩቴስ” የሚለው ቃል ያልሠለጠነ ሕዝብን ያመለክታል።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “ልባችሁን ይቆጣጠር።”
ወይም “በጸጋ።”
ወይም “ምክር።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ወይም “ኃይለኛም አትሁኑባቸው።”
ወይም “ተስፋ እንዳይቆርጡ።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
የቃላት መፍቻው ላይ “ነፍስ” የሚለውን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።