ምሳሌ 17:1-28

  • ለመልካም ነገር ክፉ አትመልስ (13)

  • “ጥል ከመነሳቱ በፊት ከአካባቢው ራቅ” (14)

  • “እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው” (17)

  • “ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኃኒት ነው” (22)

  • ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰው ንግግሩ ቁጥብ ነው (27)

17  ጠብ እያለ ትልቅ ድግስ ከተደገሰበት* ቤት ይልቅሰላም* ባለበት ደረቅ የዳቦ ቁራሽ መብላት ይሻላል።+   ጥልቅ ማስተዋል ያለው አገልጋይ አሳፋሪ ድርጊት በሚፈጽም ልጅ ላይ ሥልጣን ይኖረዋል፤ከወንድማማቾቹ እንደ አንዱ ውርስ ይካፈላል።   ማቅለጫ ለብር፣ ምድጃ ለወርቅ ነው፤+ልብን የሚመረምር ግን ይሖዋ ነው።+   ክፉ ሰው ጎጂ የሆነን ንግግር በትኩረት ያዳምጣል፤አታላይ ሰውም ተንኮለኛ የሆነን አንደበት ያዳምጣል።+   በድሃ የሚያፌዝ ሁሉ ፈጣሪውን ይሳደባል፤+በሌላው ሰው ላይ በደረሰው መከራ የሚደሰትም ሁሉ ከቅጣት አያመልጥም።+   የልጅ ልጆች* የሽማግሌዎች ዘውድ ናቸው፤አባቶችም * ለወንዶች ልጆቻቸው* ክብር ናቸው።   ለሞኝ ሰው ቀና* ንግግር አይስማማውም።+ ለገዢ* ደግሞ ሐሰተኛ ንግግር ጨርሶ አይሆነውም!+   ስጦታ ለባለቤቱ እንደከበረ ድንጋይ* ነው፤+በሄደበት ሁሉ ስኬት ያስገኝለታል።+   በደልን ይቅር የሚል* ሁሉ ፍቅርን ይሻል፤+አንድን ጉዳይ ደጋግሞ የሚያወራ ግን የልብ ጓደኛሞችን ይለያያል።+ 10  ሞኝን ሰው መቶ ጊዜ ከመግረፍ ይልቅ+ማስተዋል ያለውን ሰው አንድ ጊዜ መገሠጽ የተሻለ ውጤት ያስገኛል።+ 11  ክፉ ሰው የሚሻው ዓመፅን ብቻ ነው፤ሆኖም እሱን እንዲቀጣ ጨካኝ መልእክተኛ ይላክበታል።+ 12  የቂል ሥራ እየሠራ ካለ ሞኝ ሰው ጋር ከመገናኘት ይልቅግልገሎቿን ካጣች ድብ ጋር መገናኘት ይሻላል።+ 13  ማንኛውም ሰው ለመልካም ነገር ክፉ የሚመልስ ከሆነክፉ ነገር ከቤቱ አይጠፋም።+ 14  ጠብ መጫር ግድብን ከመሸንቆር* ተለይቶ አይታይም፤ስለዚህ ጥል ከመነሳቱ በፊት ከአካባቢው ራቅ።+ 15  ክፉውን ነፃ የሚያደርግ፣ በጻድቁም ላይ የሚፈርድ፣+ሁለቱም በይሖዋ ዘንድ አስጸያፊ ናቸው። 16  ሞኝ ሰው ጥበብን የራሱ የሚያደርግበት ልብ* ከሌለውጥበብ የሚያገኝበት መንገድ ቢኖር ምን ይጠቅማል?+ 17  እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው፤+ደግሞም ለመከራ ቀን የተወለደ ወንድም ነው።+ 18  ማስተዋል የጎደለው ሰውበባልንጀራው ፊት እጅ በመጨበጥ ዋስ* ለመሆን ይስማማል።+ 19  ጠብ የሚወድ ሁሉ በደልን ይወዳል።+ በሩን ወደ ላይ አስረዝሞ የሚሠራ ጥፋትን ይጋብዛል።+ 20  ልቡ ጠማማ የሆነ አይሳካለትም፤*+በምላሱም የሚያታልል ጥፋት ይደርስበታል። 21  የሞኝ ልጅ አባት ሐዘን ላይ ይወድቃል፤የማመዛዘን ችሎታ የጎደለው ልጅ የወለደም ደስታ አይኖረውም።+ 22  ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኃኒት ነው፤*+የተደቆሰ መንፈስ ግን ኃይል ያሟጥጣል።*+ 23  ክፉ ሰው ፍትሕን ለማዛባትበስውር* ጉቦ ይቀበላል።+ 24  ጥልቅ ግንዛቤ ባለው ሰው ፊት ጥበብ ትገኛለች፤የሞኝ ሰው ዓይን ግን እስከ ምድር ዳርቻ ይንከራተታል።+ 25  ሞኝ ልጅ በአባቱ ላይ ሐዘን ያስከትላል፤እናቱም እንድትመረር ያደርጋል።+ 26  ጻድቁን መቅጣት* መልካም አይደለም። የተከበሩ ሰዎችንም መግረፍ ትክክል አይደለም። 27  አዋቂ ሰው ንግግሩ ቁጥብ ነው፤+ጥልቅ ግንዛቤ ያለው ሰውም የተረጋጋ ነው።*+ 28  ሞኝ ሰው እንኳ ዝም ሲል እንደ ጥበበኛ ይቆጠራል፤ከንፈሮቹንም የሚዘጋ ማስተዋል እንዳለው ተደርጎ ይታያል።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ጸጥታ።”
ቃል በቃል “መሥዋዕቶች ከሞሉበት።”
ቃል በቃል “ወንዶች የልጅ ልጆች።”
ወይም “ወላጆችም።”
ወይም “ለልጆቻቸው።”
ወይም “ለተከበረ ሰው።”
ወይም “መልካም።”
ወይም “ሞገስ የሚያስገኝ ድንጋይ።”
ቃል በቃል “የሚሸፍን።”
ቃል በቃል “ውኃን ከመልቀቅ።”
ወይም “ማስተዋል።”
ወይም “ተያዥ።”
ቃል በቃል “መልካም ነገር አያገኝም።”
ወይም “ፈውስ ያስገኛል።”
ወይም “አጥንትን ያደርቃል።”
ቃል በቃል “ከሰው ጉያ።”
ወይም “መቀጫ ማስከፈል።”
ቃል በቃል “መንፈሱ ቀዝቃዛ ነው።”