በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የሕዝቅኤል መጽሐፍ

ምዕራፎች

የመጽሐፉ ይዘት

  • 1

    • ሕዝቅኤል በባቢሎን ሆኖ የአምላክን ራእዮች ተመለከተ (1-3)

    • የይሖዋ ሰማያዊ ሠረገላ ራእይ (4-28)

      • አውሎ ነፋስ፣ ደመናና እሳት (4)

      • አራት ሕያዋን ፍጥረታት (5-14)

      • አራት መንኮራኩሮች (15-21)

      • እንደ በረዶ የሚያብረቀርቅ ጠፈር (22-24)

      • የይሖዋ ዙፋን (25-28)

  • 2

    • ሕዝቅኤል የነቢይነት ተልእኮ ተሰጠው (1-10)

      • “ቢሰሙም ባይሰሙም” (5)

      • ሙሾ የተጻፈበት ጥቅልል አየ (9, 10)

  • 3

    • ሕዝቅኤል አምላክ የሰጠውን ጥቅልል እንዲበላ ታዘዘ (1-15)

    • ሕዝቅኤል ጠባቂ ሆኖ እንዲያገለግል ተሾመ (16-27)

      • ቸልተኛ መሆን የደም ዕዳ ያስከትላል (18-21)

  • 4

    • የኢየሩሳሌም ከበባ በምሳሌያዊ ሁኔታ ተገለጸ (1-17)

      • በደሉን ለ390 ቀናትና ለ40 ቀናት ይሸከማል (4-7)

  • 5

    • ኢየሩሳሌም ጥፋት እንደሚደርስባት በምሳሌያዊ ሁኔታ ተገለጸ (1-17)

      • ነቢዩ ከተላጨ በኋላ ፀጉሩን ሦስት ቦታ ይከፍለዋል (1-4)

      • ኢየሩሳሌም ከሌሎች ብሔራት የከፋ ድርጊት ፈጽማለች (7-9)

      • በሦስት መንገድ ቅጣት ይደርስባታል (12)

  • 6

    • በእስራኤል ተራሮች ላይ የተነገረ ትንቢት (1-14)

      • አስጸያፊ የሆኑት ጣዖታት ውርደት ይከናነባሉ (4-6)

      • ‘እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ’ (7)

  • 7

    • ፍጻሜው ደርሷል (1-27)

      • “በዓይነቱ ልዩ የሆነ ጥፋት” (5)

      • “ብራቸውን በየጎዳናው ይጥላሉ” (19)

      • ቤተ መቅደሱ ይረክሳል (22)

  • 8

    • ሕዝቅኤል በራእይ ወደ ኢየሩሳሌም ተወሰደ (1-4)

    • በቤተ መቅደሱ ውስጥ አስጸያፊ ነገሮች ታዩ (5-18)

      • ሴቶች ለታሙዝ አለቀሱ (14)

      • ወንዶች ፀሐይን አመለኩ (16)

  • 9

    • ስድስት ፍርድ አስፈጻሚዎችና የጸሐፊ የቀለም ቀንድ የያዘ ሰው (1-11)

      • ፍርድ ከመቅደሱ ይጀምራል (6)

  • 10

    • ከመንኮራኩሮቹ መካከል እሳት ተወሰደ (1-8)

    • የኪሩቦችና የመንኮራኩሮች መግለጫ (9-17)

    • የአምላክ ክብር ከቤተ መቅደሱ ተነስቶ ሄደ (18-22)

  • 11

    • ክፉዎቹ አለቆች ተወገዙ (1-13)

      • ከተማዋ በድስት ተመሰለች (3-12)

    • ተመልሰው እንደሚቋቋሙ ቃል ተገባላቸው (14-21)

      • “አዲስ መንፈስ” ይሰጣቸዋል (19)

    • የአምላክ ክብር ከኢየሩሳሌም ተነስቶ ሄደ (22, 23)

    • ሕዝቅኤል በራእይ ወደ ከለዳውያን ምድር ተመለሰ (24, 25)

  • 12

    • የስደት ጉዞው በምሳሌያዊ መንገድ ተገለጸ (1-20)

      • የስደተኛ ጓዝ (1-7)

      • አለቃው በጨለማ ይወጣል (8-16)

      • የጭንቀት ምግብ፣ የፍርሃት ውኃ (17-20)

    • አሳሳች የሆነው አባባል ውሸት መሆኑ ተረጋገጠ (21-28)

      • “ከተናገርኩት ቃል ውስጥ የሚዘገይ አይኖርም” (28)

  • 13

    • በሐሰተኞቹ ነቢያት ላይ የተነገረ ትንቢት (1-16)

      • በኖራ የተለሰኑ ግድግዳዎች ይፈርሳሉ (10-12)

    • በሐሰተኞቹ ሴት ነቢያት ላይ የተነገረ ቃል (17-23)

  • 14

    • ጣዖት አምላኪዎች ተወገዙ (1-11)

    • በኢየሩሳሌም ላይ ከሚወሰደው የፍርድ እርምጃ ማምለጥ አይቻልም (12-23)

      • ጻድቅ የሆኑት ኖኅ፣ ዳንኤልና ኢዮብ (14, 20)

  • 15

    • ኢየሩሳሌም፣ የማትጠቅም የወይን ተክል (1-8)

  • 16

    • አምላክ ለኢየሩሳሌም ያለው ፍቅር (1-63)

      • ተጥላ የተገኘች ልጅ (1-7)

      • አምላክ አስዋባት፤ ከእሷም ጋር የጋብቻ ቃል ኪዳን ገባ (8-14)

      • ታማኝ ሳትሆን ቀረች (15-34)

      • በአመንዝራነቷ ተቀጣች (35-43)

      • ከሰማርያና ከሰዶም ጋር ተነጻጸረች (44-58)

      • አምላክ ቃል ኪዳኑን አስታወሰ (59-63)

  • 17

    • የሁለቱ ንስሮችና የወይን ተክሉ እንቆቅልሽ (1-21)

    • ለጋ የሆነው ቀንበጥ የሚያምር አርዘ ሊባኖስ ሆነ (22-24)

  • 18

    • እያንዳንዱ በገዛ ኃጢአቱ ይጠየቃል (1-32)

      • ኃጢአት የምትሠራ ነፍስ ትሞታለች (4)

      • ልጅ በአባቱ ኃጢአት አይጠየቅም (19, 20)

      • በክፉዎች ሞት ደስ አይሰኝም (23)

      • ንስሐ መግባት ሕይወት ያስገኛል (27, 28)

  • 19

    • ስለ እስራኤል አለቆች የተነገረ ሙሾ (1-14)

  • 20

    • የእስራኤላውያን ዓመፅ (1-32)

    • እስራኤላውያን ተመልሰው እንደሚቋቋሙ የተገባላቸው የተስፋ ቃል (33-44)

    • በደቡብ ላይ የተነገረ ትንቢት (45-49)

  • 21

    • የአምላክ የፍርድ ሰይፍ ተመዘዘ (1-17)

    • የባቢሎን ንጉሥ በኢየሩሳሌም ላይ ጥቃት ይሰነዝራል (18-24)

    • መጥፎው የእስራኤል አለቃ ከቦታው ይነሳል (25-27)

      • ‘አክሊሉን አንሳ’ (26)

      • “ሕጋዊ መብት ያለው እስኪመጣ ድረስ” (27)

    • በአሞናውያን ላይ የተመዘዘ ሰይፍ (28-32)

  • 22

    • ኢየሩሳሌም፣ የደም ዕዳ ያለባት ከተማ (1-16)

    • እስራኤል ከላይ እንደሚሰፍ የማይረባ ቆሻሻ ናት (17-22)

    • የእስራኤል ሕዝብና መሪዎች ተወገዙ (23-31)

  • 23

    • ታማኝ ያልሆኑ ሁለት እህትማማቾች (1-49)

      • ኦሆላ ከአሦር ጋር አመነዘረች (5-10)

      • ኦሆሊባ ከባቢሎንና ከግብፅ ጋር አመነዘረች (11-35)

      • በሁለቱ እህትማማቾች ላይ የተላለፈ የቅጣት ፍርድ (36-49)

  • 24

    • እንደዛገ ድስት የሆነችው ኢየሩሳሌም (1-14)

    • የሕዝቅኤል ሚስት ሞት እንደ ምልክት ሆኖ ያገለግላል (15-27)

  • 25

    • በአሞን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-7)

    • በሞዓብ ላይ የተነገረ ትንቢት (8-11)

    • በኤዶም ላይ የተነገረ ትንቢት (12-14)

    • በፍልስጤም ላይ የተነገረ ትንቢት (15-17)

  • 26

    • በጢሮስ ላይ የተነገረ ትንቢት (1-21)

      • “የመረብ ማስጫ ቦታ” (5, 14)

      • ድንጋዮቿና አፈሯ ወደ ባሕር ይጣላሉ (12)

  • 27

    • ስለሰመጠው የጢሮስ መርከብ የተነገረ ሙሾ (1-36)

  • 28

    • በጢሮስ ንጉሥ ላይ የተነገረ ትንቢት (1-10)

      • “እኔ አምላክ ነኝ” (2, 9)

    • ስለ ጢሮስ ንጉሥ የተነገረ ሙሾ (11-19)

      • “በኤደን ነበርክ” (13)

      • “የተቀባህ፣ የምትጋርድ ኪሩብ” (14)

      • ‘ዓመፅ ተገኘብህ’ (15)

    • በሲዶና ላይ የተነገረ ትንቢት (20-24)

    • እስራኤል ተመልሳ ትቋቋማለች (25, 26)

  • 29

    • በፈርዖን ላይ የተነገረ ትንቢት (1-16)

    • ግብፅ ለባቢሎን ካሳ ሆና ትሰጣለች (17-21)

  • 30

    • በግብፅ ላይ የተነገረ ትንቢት (1-19)

      • ናቡከደነጾር ጥቃት እንደሚሰነዝር ትንቢት ተነገረ (10)

    • የፈርዖን ክንድ ተሰበረ (20-26)

  • 31

    • በግዙፍ አርዘ ሊባኖስ የተመሰለችው ግብፅ ትወድቃለች (1-18)

  • 32

    • ስለ ፈርዖንና ስለ ግብፅ የተነገረ ሙሾ (1-16)

    • ግብፅ ካልተገረዙት ጋር ትቀበራለች (17-32)

  • 33

    • የጠባቂው ኃላፊነቶች (1-20)

    • ኢየሩሳሌም መውደቋ ተነገረ (21, 22)

    • በፍርስራሽ ውስጥ ለሚኖሩ የተላለፈ መልእክት (23-29)

    • ሰዎች መልእክቱን ሰምተው በተግባር አያውሉትም (30-33)

      • ሕዝቅኤል “የፍቅር ዘፈን” ሆነላቸው (32)

      • “በመካከላቸው ነቢይ እንደነበረ ያውቃሉ” (33)

  • 34

    • በእስራኤል እረኞች ላይ የተነገረ ትንቢት (1-10)

    • ይሖዋ በጎቹን ይንከባከባል (11-31)

      • ‘አገልጋዬ ዳዊት’ እረኛቸው ይሆናል (23)

      • “የሰላም ቃል ኪዳን” (25)

  • 35

    • በሴይር ተራሮች ላይ የተነገረ ትንቢት (1-15)

  • 36

    • ስለ እስራኤል ተራሮች የተነገረ ትንቢት (1-15)

    • የእስራኤል ተመልሶ መቋቋም (16-38)

      • ‘ታላቅ ስሜን እቀድሰዋለሁ’ (23)

      • “እንደ ኤደን የአትክልት ስፍራ” (35)

  • 37

    • የደረቁ አጥንቶች የሞሉበት ሸለቆ ራእይ (1-14)

    • አንድ ላይ የሚያያዙ ሁለት በትሮች (15-28)

      • በአንድ ንጉሥ የሚመራ አንድ ብሔር (22)

      • ዘላለማዊ የሰላም ቃል ኪዳን (26)

  • 38

    • ጎግ በእስራኤል ላይ የሚሰነዝረው ጥቃት (1-16)

    • በጎግ ላይ የሚነደው የይሖዋ ቁጣ (17-23)

      • ‘ብሔራት እኔ ይሖዋ እንደሆንኩ ያውቃሉ’ (23)

  • 39

    • በጎግና በወታደሮቹ ላይ የሚደርስ ጥፋት (1-10)

    • በሃሞን ጎግ ሸለቆ የሚፈጸም ቀብር (11-20)

    • የእስራኤል መልሶ መቋቋም (21-29)

      • የአምላክ መንፈስ በእስራኤል ላይ ይፈስሳል (29)

  • 40

    • ሕዝቅኤል በራእይ ወደ እስራኤል ተወሰደ (1, 2)

    • ሕዝቅኤል አንድ ቤተ መቅደስ በራእይ አየ (3, 4)

    • ግቢዎቹና በሮቹ (5-47)

      • በውጭ በኩል ያለው የምሥራቁ በር (6-16)

      • ውጨኛው ግቢ፤ ሌሎች በሮች (17-26)

      • የውስጠኛው ግቢና በሮች (27-37)

      • የቤተ መቅደሱ አገልግሎት የሚከናወንባቸው ክፍሎች (38-46)

      • መሠዊያው (47)

    • የቤተ መቅደሱ በረንዳ (48, 49)

  • 41

    • በቤተ መቅደሱ ውስጥ የሚገኘው መቅደስ (1-4)

    • ግንቡና በጎን በኩል ያሉት ክፍሎች (5-11)

    • በምዕራብ በኩል ያለው ሕንፃ (12)

    • ሕንፃዎቹ ተለኩ (13-15ሀ)

    • ውስጠኛው መቅደስ (15ለ-26)

  • 42

    • የመመገቢያ ክፍሎቹ ሕንፃዎች (1-14)

    • የቤተ መቅደሱ አራት ጎኖች ተለኩ (15-20)

  • 43

    • የይሖዋ ክብር ቤተ መቅደሱን ሞላው (1-12)

    • መሠዊያው (13-27)

  • 44

    • የምሥራቁ በር እንደተዘጋ ይኖራል (1-3)

    • የባዕድ አገር ሰዎችን በተመለከተ የወጡ ደንቦች (4-9)

    • ሌዋውያንንና ካህናትን በተመለከተ የወጡ ደንቦች (10-31)

  • 45

    • መዋጮ ሆኖ የተሰጠው ቅዱስ ስፍራና ከተማዋ (1-6)

    • የአለቃው ድርሻ (7, 8)

    • አለቆቹ በሐቀኝነት መሥራት ይጠበቅባቸዋል (9-12)

    • የሕዝቡ መዋጮና አለቃው (13-25)

  • 46

    • በተወሰኑ ወቅቶች የሚቀርቡ መባዎች (1-15)

    • አለቃው ንብረቱን ውርስ አድርጎ ይሰጣል (16-18)

    • መባዎች የሚቀቀሉባቸው ቦታዎች (19-24)

  • 47

    • ከቤተ መቅደሱ የሚፈስ ጅረት (1-12)

      • የውኃው ጥልቀት እየጨመረ ሄደ (2-5)

      • የሙት ባሕር ውኃ ይፈወሳል (8-10)

      • ረግረጋማ ቦታዎች አይፈወሱም (11)

      • ለምግብነትና ለፈውስ የሚያገለግሉ ዛፎች (12)

    • የምድሪቱ ወሰኖች (13-23)

  • 48

    • ምድሪቱ ተከፋፍላ ተሰጠች (1-29)

    • የከተማዋ 12 በሮች (30-35)

      • “ይሖዋ በዚያ አለ” ተብላ የተጠራችው ከተማ (35)