በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

JW LIBRARY

የእልባት አጠቃቀም—iOS

የእልባት አጠቃቀም—iOS

JW Library ላይ እልባት ለማድረግ የሚያስችለው ገጽታ በታተመው ጽሑፍ ላይ ንባብህን ያቆምክበትን ቦታ ለማስታወስ ከምታደርገው እልባት ጋር ተመሳሳይ ነው። በJW Library ላይ የሚገኘው እያንዳንዱ ጽሑፍ 10 ዓይነት እልባቶች አሉት።

እልባቶችን ለመጠቀም ከታች ያሉትን መመሪያዎች ተከተል፦

 አዲስ እልባት አድርግ

በአንድ ርዕስ፣ ምዕራፍ፣ አንቀጽ ወይም ጥቅስ ላይ እልባት ማድረግ ትችላለህ።

በአንድ ርዕስ ወይም ምዕራፍ ላይ እልባት ለማድረግ የእልባት ምልክቱን ተጫን። ከዚያም ለከፈትከው ጽሑፍ የሚሆኑ እልባቶች ዝርዝር ይወጣሉ። ያለህበት ርዕስ ወይም ምዕራፍ ላይ እልባት ለማድረግ ነፃ የሆነውን የእልባት ምልክት ተጫን።

በአንድ አንቀጽ ወይም ጥቅስ ላይ እልባት ለማድረግ መጀመሪያ አንቀጹን ወይም ጥቅሱን ተጫን፤ ከዚያም ስትጫን በሚወጣው ማውጫ ላይ ያለውን የእልባት ምልክት ተጫን።

 እልባት ክፈት

እልባት ያደረግክበትን ቦታ ለማግኘት እልባቱ የሚገኝበትን ጽሑፍ ከፍተህ የእልባት ምልክቱን ተጫን። ከዚያም የምትፈልገውን እልባት ምረጥ።

 እልባቶችን አስተካክል

እልባት ካደረግክ በኋላ ልታጠፋው ወይም በሌላ ልትተካው ትችላለህ።

  • እልባቱን ለማጥፋት የእልባት ምልክቱን ተጫን፤ ከዚያም ማጥፋት የምትፈልገውን የእልባት ምልክት ከግራ ወደ ቀኝ አንሸራት። ከዚያም አጥፋ የሚለውን ምልክት ተጫን።

  • እልባቱን በሌላ ለመተካት የእልባት ምልክቱን ተጫን፤ ከዚያም መተካት የምትፈልገውን እልባት ከግራ ወደ ቀኝ አንሸራት። ከዚያም ተካ የሚለውን ተጫን። እልባቱ አሁን በመረጥከው ቦታ ላይ ይሆናል። ይህም በምታነበው ጽሑፍ ላይ ያቆምክበትን ቦታ ለማወቅ ያስችልሃል። ለምሳሌ በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብብ ያቆምክበትን ቦታ ለማወቅ ይረዳሃል።

ይህ ገጽታ የወጣው ግንቦት 2014 ሲሆን እትሙ JW Library 1.2 ነው፤ ይህ እትም በiOS 6.0 ወይም ከዚያ በኋላ ያለ ሶፍትዌር በተጫነላቸው መሣሪያዎች ላይ ይሠራል። እነዚህን ገጽታዎች ማግኘት ካልቻልክ “JW Library መጠቀም ጀምር—iOS” በሚለው ርዕስ ውስጥ አዳዲስ ገጽታዎች በሚለው ሥር ያሉትን መመሪያዎች ተከተል።